=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
=<({አል-ቁርአን 113:1-3})>=
1 በጊዜያት እምላለሁ።
2 በእርግጥ ሰው ሁሉ በኪሳራ ውስጥ ነው።
3 እነዚያ ያመኑት ፣ መልካም ስራን የሰሩት ፣ በእውነት እና በትዕግስት አደራ የተባባሉት ብቻ ሲቀሩ።
ምስጋና ለአለማት ጌታ ለሆነው ለአሏህ ይገባው። አሏህ የመራውን ማንም አያጠምም፤ አሏህ ያጠመመውንም ማንም አይመራም። የአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ሰላምና እዝነት በረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ላይ ፣ በቤተሰቦቻቸው ፣ በሶሃቦቻቸው እንዲሁም የሳቸውን ፈለግ እስከ እለተ ቂያማ ድረስ በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን።
አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካቱህ! ውድ የወጣቱ ተልዕኮ እንግዶች የአሏህ ሰላም ፣ እዝነና በረከት በእናንተ ላይ ይሁን።
ይህ የሞባይል ሳይት የወጣቱ ተልእኮ በሚል አድራሻ የተዘጋጀ ሲሆን ሳይቱ ሙሉ በሙሉ ኢስላማዊ የሆነ ነው። የአድራሻውን ስም እንድሰጥ ምክኒያት የሆነኝ የራሴ የእድሜ ክልል እና ወጣቶች በሙስሊሙ ኡማ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን የነቃ ተሳትፎ ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው። ሳይቱን ለመፍጠር ምክኒያት የሆነኝ ደግሞ 12ኛ ክፍል የነደፍኳቸው ግቦች ናቸው። ሌላው ያነሳሳኝ ነገር አብዛሃኛው የማህበረሰባችን ክፍል ከአሊሞች ጋር ቁጭ ብሎ ከመማር እያፈገፈገ ፣ አሊሞችም በየቦታው ቀያቸውን ጥለው እየተሰደዱ ፣ ወጣቱ ክፍልም ከማወቅ ከመማር እየራቀ ፣ የማንበብ ባህሉ እየደከመ ፣ ከእውቀት ይልቅ ጨዋታ አሉቧልታ ያአሉ ወሬ እጥቅቶት የእውቀት ድሃ ሆኖ ሲንከራተት በማየቴ እና ወጣቱ ክፍል ኦንላይን ላይ የሚያዘወትር በመሆኑ ኡማውን ኦንላይንም ሆነ በተለያዩ የህትመት ውጤቶች ማገልገል እንዳለብኝ ስለተሰማኝ ነው።
ከላይ እንደተገለፀው ሳይቱ ሙሉ በሙሉ ኢስላማዊ ሲሆን ከማንኛውም አይነት ሃይማኖታዊ ክፍፍል ወይም ቡድንተኝነት የፀዳ ነው። ለዚህም ቁንርንና ሱናን ተንተርሶ አሏህ በሰጠን ቁርአናዊ መጠሪያ ሙስሊም በሚለው ስም የተብቃቃ ነው። ዋና አላማው "ወደ ጌታህ በጥበብና በመልካም ግሳፄ ጥራ" የሚለውን መለኮታዊ ራዕይ እና "ከእኔ የሰማችሁትን አንዲትም አንቀፅ(አረፍተ ነገር) ብትሆን አስተላልፉ" የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ ተመርኩዞ የኢስላምን ትክክለኛ መልእክት ለሁሉም የሰው ልጆች ማድረስ ፣ የአሏህንና የረሱልን(ሰ.ዐ.ወ) ንግግር የበላይ ማድረግ ፣ ኡማውን በድህረገፅና በሶፍትዌር ደቨሎፕመንትና ፕሮግራሚንግ ማገልገል ፣ የአንብብ ትውልድ ለንባብ እና ለእውቀት ትኩረት እንዲሰጥ ማገዝ ፣ በከፊልም ቢሆን ስለዲኑ የሚያውቅ ወጣት ማፍራት ፣ ኡማውን በቁርአን እና በሱና ገመድ ማስተሳሰር ፣ ስለ ኢስላም የምንማርባቸውን መንገዶች ማመቻቸት ነው።
በዚህ የሞባይል ሳይት ውስጥ ከተካተቱ ነገሮች መካከል ኢስላማዊ ጽሁፎች ፣ መጽሐፎች ፣ ቪዲዮችና ኦዲዩ ዳዕዋወች ፣ ታሪኮች ፣ ግጥሞች ፣ ኢስላሚክ ፎቶዎች ፣ ጥያቄና መልስ ፣ ኢስላማዊ የመረጃ መረብ ሊንኮች ፣ ኢስላማዊ የእይታ መስኮት ሞገዶች ወ.ዘ.ተ ተካተውበታል። ከዚህም በተጨማሪ አላዋቂ ሙስሊሞችና ካፊሮች ለሚያነሱት የተሳሳቱ አመለካከቶች ምላሽ ይሰጣል። የኢስላምን መልእክት በማሰራጨት ፣ ሼር በማድረግ እና የነቃ ተሳትፏችሁን በማሳየት የዚህ ተልእኮ አንዱ አካል ይሁኑ።
ማንኛውም አይነት አስተያየት ፣ ትችትና ነቀፌታ ካለዎት በኢሜል አድራሻየ ahmedyesuf29@gmail.com ላይ ሊፅፍልኝ ወይም ደግሞ 251927790323 ላይ ሊደወሉልኝ ይችላሉ። ተጨማሪ የወጣቱ ተልዕኮ ኢስላማዊ መጣጥፎችን ለማግኘት http://youth-mission.mobie.in ይጎብኙ። ጀዛኩሙለህ ኸይረን ከሲረን!
አድራሻችን
መስራች: አህመድ የሱፍ
ሰሜን ወሎ ወልዲያ
13/05/2005
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|